ዘፍጥረት 31:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም አባትዋን፥ “ፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፥ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። እርሱም ፈለገ፥ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሔልም አባቷን፣ “በፊትህ ተነሥቼ መቆም ስላልቻልሁ፣ ጌታዬ አትቈጣ፤ የወር አበባዬ መጥቶ ነው።” አለችው፤ ስለዚህ በረበረ፤ የጣዖታቱን ምስል ግን ማግኘት አልቻለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሔልም አባቷን “ጌታዬ በወር አበባዬ ምክንያት መነሣት ስላልቻልኩ ቅር አትሰኝብኝም” አለችው። ላባ በሁሉ ስፍራ ፈልጎ ጣዖቶቹን ማግኘት አልቻለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም አባቷን፥ “ጌታዬ በፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ የአቀለልሁህ አይምሰልህ፤ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። ላባም የራሔልን ድንኳን በረበረ፤ ነገር ግን ጣዖቶቹን አላገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም አባትዋን፦ በፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፤ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና አለችው። እርሱም ፈለገ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም። |
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
“ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት ከሰውነቷም ውስጥ የሚፈስሰው ነገር ደም ቢሆን፥ በወር አበባዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።