ዘፍጥረት 31:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉዳት አደርስብህ ዘንድ ኃይል ነበረኝ፥ ነገር ግን የአባታችሁ አምላክ ትናንት፥ ‘ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ’ ብሎ ነገረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጐዳችሁ እችል ነበር፤ ዳሩ ግን ባለፈው ሌሊት የአባታችሁ አምላክ ‘ያዕቆብን፣ ክፉም ሆነ ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ’ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጒዳት ላደርስብህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ ‘ያዕቆብን፥ ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በአንተ ላይ ክፉ ማድረግ በቻልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአባትህ አምላክ ትናንት፦ በያዕቆብ ላይ ክፉ እንዳታደርግ ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉ አደርግባችሁ ዘንድ ኃይል ነበረኝ፤ ነገር ግን የአባታችሁ አምላክ ትናንት፦ ያዕቆብን በክፉ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ። |
እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፦ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፥
የአባቴ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት፥ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ፥ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፥ እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ልፋት አየ፥ ትናንትና ሌሊትም ገሠጸህ።”
“ጌታ ሆይ! ማን ነህ?” አለው። እርሱም “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል፤” አለው።