ዘፍጥረት 31:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዘመዶቹም ጋር ሆኖ የሰባት ቀን መንገድ ያህል ተከተለው፥ ከዚያም በገለዓድ ተራራማ አገር ላይ አገኛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባ ዘመዶቹን ይዞ ተነሣ፤ ያዕቆብንም ሰባት ቀን ተከታትሎ ገለዓድ በተባለ ኰረብታማ አገር ደረሰበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዘመዶቹ ጋር ሆኖ ያዕቆብን ተከታተለው፤ ሰባት ቀን ከተጓዘ በኋላ ገለዓድ በተባለው ተራራማ አገር ላይ ሊደርስበት ተቃረበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ወንድሞቹን ሁሉ ይዞ የሦስት ቀን መንገድ ተከተላቸው፤ በገለዓድ ተራራም ላይ አገኛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንድሞቹም ጋር ሆኖ የሰባት ቀን መንገድ ያህል ተከተለው በገለዓድ ተራራም ላይ ደረሰበት |
እንዲህም አለ፦ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።”
በነዚያም ቀኖች፥ ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወንድሞቹ ወጣ፥ የሥራቸውንም መከራ ተመለከተ፤ የግብጽም ሰው ከወንድሞቹ አንድ የሆነውን ዕብራዊ ሰው ሲመታ አየ።