ዘፍጥረት 31:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ለመሄድ ማቀዱን ሳይነግረው ሶርያዊውን ላባን ከድቶ ኮበለለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ቢሆን፣ መኰብለሉን ለሶርያዊው ለላባ ሳይገልጥለት በመቅረቱ አታልሎታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ መሄዱን ለላባ ሳይገልጥለት አታሎት ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ነገሩን ከሶርያዊው ከላባ ሰወረ፤ እንደሚሄድም አልነገረውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም የሶርያውን ሰው ላባን ከድቶ ኮበለለ መኮብለሉን፥ አልነገረውም። |
አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።