La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 30:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፥ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፥ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ልያም፣ “ምንኛ ደስተኛ ሆንሁ ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛዋ ይሉኛል” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ አወጣችለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልያም “እጅግ ደስ ብሎኛል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ሁሉ ‘ደስተኛዋ ሴት!’ ይሉኛል” ስትል ስሙን አሴር ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልያም፥ “እኔ ብፅ​ዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛ​ልና” አለች፤ ስሙ​ንም አሴር ብላ ጠራ​ችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 30:13
8 Referencias Cruzadas  

የልያ ባርያ ዘለፋም ዳግመኛ ለያዕቆብ ወንድ ልጅን ወለደች።


የልያ ባርያ የዚልፋ ልጆችም፥ ጋድ፥ አሴር ናቸው። እነዚህ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።


የአሴር ልጆች፦ ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ናቸው። እኅታቸው ሤራሕ ትባላለች። የበሪዓ ልጆች ደግሞ ሔቤርና ማልኪኤል ናቸው።


የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው፥ ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል።


ልጆችዋ ይነሣሉ፥ ምስጉን ነሽ ይሏታል፥ ባሏ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፦


ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ አንዲት ናት፥ ለእናትዋ አንዲት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው ብፅዕት አሉአት፥ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኑአት።


እኔን ዝቅተኛይቱን አገልጋይ ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤