ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።
ዘፍጥረት 29:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፥ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፥ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እንደ ገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት “ከእንግዲህ ባሌ ያቀርበኛል” አለች፤ ስለዚህ ሌዊ ብላ ጠራችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል” ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ “ከእንግዲህ ወዲህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፤ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፤ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። |
ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።
ሦስተኛም ቀን በሆነ ጊዜ እጅግ ቆስለው እያሉ፥ የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ፥ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፥