ዘፍጥረት 27:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንድምህ ቁጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፥ ከዚያም ልኬ አስመጣሃለሁ፥ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ቍጣው በርዶለት ያደረግህበትን ከረሳ በኋላ፣ እንድትመለስ እልክብህና ትመጣለህ። ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ለምን ልጣ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊጣውም ሲበርድ ያደረግህበትን ነገር ይረሳል፤ ከዚያ በኋላ ሰው ልኬ አስመጣሃለሁ፤ ለምን ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ልጣ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያደረግህበትንም እስኪረሳው ድረስ፤ በአንድ ቀን ሁለታችሁን እንዳላጣ፥ ከዚያም ልኬ አመጣሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህ ቍጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህባትንም እስኪረሳው ድረስ ከዚይም ልኬ አስመጣሃለሁ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ? |
ያዕቆብም አባቱን አለው፦ “የበኩር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፥ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፥ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ።”
አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም፤” አሉ።