ዘፍጥረት 25:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጀመሪያም የወጣው ቀይ ነበረ፥ ሁለንተናውም ጠጉር ለብሶ ነበር፥ ስለዚህ ዔሳው ብለው ጠሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጀመሪያ የተወለደው መልኩ ቀይ፣ ሰውነቱም በሙሉ ጠጕር የለበሰ ነበር፤ ስለዚህ ስሙ ዔሳው ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ልጅ መልኩ ቀይ፥ ሰውነቱ ጠጒራም ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ተባለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበኵር ልጅዋም ወጣ፤ እንደ ጽጌረዳም ቀይ ነበረ፤ ሁለንተናውም ጠጕራም ነበር፤ ስሙንም ዔሳው ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ ሁለንትናውም ጠጕር ለብሶ ነበር፤ ስሙም ዔሳው ተባለ። |
እንዲህም ሆነ፥ ይስሐቅ ሸምግሎ ዐይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው እርሱ፥ “እነሆ አለሁ” አለው።
ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።
ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ የደረሰብንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤