ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገኔም ሂድ፥ ለልጄም ሚስትን ውሰድለት።’
ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት፣ ወደ ገዛ ወገኖቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት አምጣለት።’
ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገኖቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት ምረጥ፤
ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገኔም ሂድ፤ ለልጄም ከዚያ ሚስትን ውሰድለት።
ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገኔም ሂድ ለልጄም ሚስትን ውሰድለት።
እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።
ጌታዬም እንዲህ ሲል አማለኝ፦ ‘እኔ ካለሁበት አገር ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስትን አትውሰድ
ጌታዬንም፦ ‘ሴቲቱ ምናልባት ባትከተለኝሳ?’ አልሁት።
ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ተወላጆቼ ትሄዳለህ፥ ለልጄ ለይስሐቅም ሚስትን ትወስድለታለህ።”
ላባም በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር፥ ራሔልም የአባትዋን ቤት ጣዖቶች ሰረቀች።