ሣራም የጌታዬ ሚስት በእርጅናው ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፥ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው።
የጌታዬ ሚስት ሣራ በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለልጁ ሰጥቶታል።
የጌታዬ ሚስት ሣራ በእርጅናዋ ዘመን ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለዚሁ ልጅ አውርሶታል።
የጌታዬ የአብርሃም ሚስት ሣራም በእርጅናዋ ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፤ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው።”
ሣራም የጌታዬ ሚስት በእርጅናዋ ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፤ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው።
አብርሃምንም “ይህችን ባርያ ከነልጇ አባርራት፥ የዚህች ባርያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና” አለችው።
አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፥
መቶ ዓመት ሆኖት ሳለ ምውት የሆነውን የራሱን አካልና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆን አስቦ በእምነት አልደከመም፤