La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፈጥናም ውኃውን ከእንስራዋ በማጠጫው ውስጥ ገለበጠችው፥ ደግሞም ልትቀዳ ወደ ጉድጓዱ ሮጠች፥ ለግመሎቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፈጥናም በእንስራው ውስጥ የነበረውን ውሃ በገንዳ ውስጥ ገለበጠች፤ እየሮጠች ከጕድጓዱ ውሃ እያመላለሰች ግመሎቹ እስኪበቃቸው ድረስ አጠጣቻቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወዲያውኑ በእንስራዋ የያዘችውን ውሃ ግመሎቹ በሚጠጡበት ገንዳ ላይ ገልብጣ ግመሎቹ ሁሉ ጠጥተው እስከሚረኩ ድረስ እየተጣደፈች ከጒድጓድ ውሃ መቅዳት ቀጠለች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈጥ​ናም ውኃ​ውን ከእ​ን​ስ​ራዋ በማ​ጠ​ጫው ውስጥ ገለ​በ​ጠ​ችው፤ ደግ​ሞም ልት​ቀዳ ወደ ጕድ​ጓዱ ሮጠች፤ ለግ​መ​ሎ​ቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈጥናም ውኃውን ከእንስራዋ በማጠጫው ውስጥ ገለበጠችው ደግሞም ልትቀዳ ወደ ጕድጓዱ ሮጠች ለግመሎቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 24:20
3 Referencias Cruzadas  

እርሱንም ካጠጣች በኋላ፦ “ለግመሎችህ ደግሞ ሁሉም እስኪረኩ ድረስ ውኃ እቀዳለሁ” አለች።


ሰውዬውም ትክ ብሎ ይመለከታት ነበር፥ እግዚአብሔር መንገዱን አቅንቶለት እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ለማወቅም ዝም አለ።


ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከ እንዲህም አለ፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥