ዘፍጥረት 23:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታዬ ሆይ፥ እኔን ስማኝ፥ የአራት መቶ ሰቅል ዋጋ መሬት በእኔና በአንተ መካከል ምንድነው? እንግዲህ ሬሳህን ቅበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታዬ ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋማ አራት መቶ ጥሬ ብር ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በአንተ መካከል ምን ቁም ነገር አለው? ይልቅስ ሬሳህን ቅበርበት” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጌታዬ የመሬቱ ዋጋ አራት መቶ ብር ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በእናንተ መካከል ምንድን ነው? ይልቅስ የሚስትህን አስከሬን እዚህ ቅበር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአራት መቶ ምዝምዝ ብር ዋጋ ምድር በእኔና በአንተ መካከል ምንድን ነው? እንግዲህ ሬሳህን በዚያ ቅበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የአራት መቶ ሰቅል ዋጋ ምድር በእኔና በአንተ መካክለ ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር። |
በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።