La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና፥ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለ ሆነ፥ ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰባ​ተ​ኛ​ዋን ቀን ባረ​ካት፤ ቀደ​ሳ​ትም፤ ሊፈ​ጥ​ረው ከጀ​መ​ረው ሥራ ሁሉ በእ​ር​ስዋ ዐር​ፎ​አ​ልና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ሰባተኚውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረዉ ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 2:3
22 Referencias Cruzadas  

እግዚእብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን።


እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።


ጌታ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን፥ የሰማያትና ምድር ልደት፥ በተፈጠሩበት ጊዜ፥ እንዲህ ነበር።


ቅዱስ ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፥ ትእዛዞችን፥ ሥርዓቶችንና ሕግን በባርያህ በሙሴ በኩል አዘዝሃቸው።


ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ በሬህና አህያህ እንዲያርፉ የባርያህ ልጅና መጻተኛውም ዕረፍት እንዲሆንላቸው በሰባተኛው ቀን ዕረፍ።


ስድስት ቀን ትሠራለህ፥ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ፥ በምታርስበትና በምታጭድበት ጊዜ ታርፋለህ።


የጌታ በረከት ሀብታም ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርሷ ጋር አይጨምርም።


የምቀድሳቸውም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት ይሆኑ ዘንድ ሰንበታቴን ሰጠኋቸው።


“ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረግበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለጌታ ሰንበት ነው።


ደግሞ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሯል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤


ተመልሰውም ሽቱና ቅባት አዘጋጁ። በሰንበትም ዕለት ሕጉ እንዲሚያዘው ዐረፉ።