ዘፍጥረት 18:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፥ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ አሕዛብ ሁሉ በርሱ ይባረካሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአብርሃም ዘር ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ በእርሱም አማካይነት በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፤ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። |
ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።
መጽሐፍም፥ እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፥ “አሕዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ፤” ብሎ አስቀድሞ ለአብርሃም ወንጌልን ሰበከለት።