አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
ዘፍጥረት 17:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ፥ ከአብርሃም ቤተሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ፥ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ዕለት አብርሃም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ልጁን እስማኤልን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትንና ከውጭ በገንዘቡ የገዛቸውን ወንዶች በሙሉ ሸለፈታቸውን ገረዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም በዚያኑ ቀን ልጁን እስማኤልን ገረዘው፤ እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የተወለዱና ከውጪ የተገዙ ባሪያዎች ሳይቀሩ፥ በቤቱ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ልጁን ይስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በወርቅም የገዛውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ። የሥጋቸውንም ቍልፈት እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ልጁን እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ ከአብርሃም ቤተሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔ እንዳለው በዚያው ቀን ገረዘ። |
አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።
ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፤ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።