እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።”
ዘፍጥረት 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ኑ! እንውረድ፥ እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑ እንውረድ፤ እርስ በርሳቸውም እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኑ! እንውረድና እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑ እንውረድ፤ አንዱ የሌላውን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑ፥ እንውረድ፤ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚይ እንደባልቀው። |
እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።”
ከእነዚህም በባሕር ዳርቻ ሕዝቦች፥ ሁሉም በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፍለው የሚኖሩ የያፌት ልጆች ዘር ናቸው።
ከዚያም ጌታ እግዚአብሔርም፥ “እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፥ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘለዓለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር”፥ አለ።
ጌታም እንዲህ አለው፦ “የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳ ወይም ደንቆሮ ወይም የሚያይ ወይም ዕውር ያደረገ ማን ነው? እኔ ጌታ አይደለሁምን?
የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ፥ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ጽኑ ጥንታዊ ሕዝብ ነው፥ ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።
እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን በአንድነት በተሰበሰቡበት፥ ሁሉም በልሳን በመናገር ላይ እያሉ፥ እንግዶች ወይም የማያምኑ ሰዎች ወደ ጉባኤው ቢገቡ፥ አብደዋል አይሉምን?