ገላትያ 5:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስ የምንኖር ከሆንን በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንፈስ የምንኖር ከሆን፣ በመንፈስ እንመላለስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመንፈስ የምንኖር ከሆንን በመንፈስ እንመራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም በመንፈስ እንኑር፤ በመንፈስም እንመላለስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። |
እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ላልሆነ፥ ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንድንሆን አበቃን፤ ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።
ወንጌል ለሙታን ሳይቀር የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ ስለዚህ እንደ ሰው ሁሉ በሥጋ ይፈረድባቸዋል፤ በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይኖራሉ።
ከሦስቱ ቀን ተኩልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።