ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።
ገላትያ 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን ግን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያህል የማታስተውሉ ናችሁን? በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ፍጹም ለመሆን ትጥራላችሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእግዚአብሔር መንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋዊ ጥረት መፈጸም ትፈልጋላችሁ፤ ለካ እስከዚህ ድረስ ሞኞች ናችሁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህን ሰነፎች ናችሁን? የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ከጀመራችሁ በኋላ የሥጋን ሕግ ልትሠሩ ትመለሳላችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? |
ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።