ገላትያ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ከዐሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፥ ቲቶንም ከእኔ ጋር ይዤው ሄድሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዐሥራ አራት ዓመት በኋላም፣ ዳግመኛ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤ በዚህ ጊዜ ከበርናባስ ጋራ ነበርሁ፤ ቲቶንም ይዤው ሄጄ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዐሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ ሄድኩ፤ ቲቶንም ከእኔ ጋር ይዤው ሄጄ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዐሥራ አራት ዓመትም በኋላ ከበርናባስ ጋር እንደ ገና ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤ ቲቶንም ይዠው ሄድሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያ ወዲያ ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ከበርናባስ ጋር ቲቶን ደግሞ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም ሁለተኛ ወጣሁ፤ |
አይሁድ ግን የሚያመልኩትን የከበሩትንም ሴቶችና የከተማውን መኳንንት አወኩ፤ በጳውሎስና በበርናባስም ላይ ስደትን አስነሥተው ከአገራቸው አወጡአቸው።
ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን።
ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፥ እናንተን ለማገልገል አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖር፥ የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።
የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው፥ ምሰሶዎች መስለው የሚታዩ ያዕቆብ፥ ኬፋና ዮሐንስ፥ እነርሱ ወደ ተገረዙት እኛ ወደ አሕዛብ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ የኅብረት ቀኝ እጃቸውን ሰጡን፤
“ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት፤” የሚል ትእዛዝ የተቀበላችሁለት የበርናባስ የወንድሙ ልጅ ማርቆስ እንዳረገው እንዲሁ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።