ዕዝራ 7:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በላይ ለአምላክህ ቤት የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ ከንጉሡ ቤተ መዛግብት ውሰድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በላይ ለአምላክህ ቤተ መቅደስ ለመስጠት የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ከንጉሡ ግምጃ ቤት መውሰድ ትችላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤተ መቅደሱ መገልገያ የሚያስፈልግህንም ሌላውን ነገር ሁሉ ከቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ልትወስድ ትችላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በላይ ለማውጣት የሚያስፈልግህን ለአምላክህ ቤት የሚያሻውን ነገር ከንጉሡ ቤተ መዛግብት ስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በላይ ለማውጣት የሚያስፈልግህን ለአምላክ ቤት የሚያሻውን ነገር ከንጉሡ ቤተ መዛግብት አውጣ። |