ከአንተ ዘንድ የመጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጡ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ዓመፀኛይቱንና ክፉይቱን ከተማ በመስራት፥ ቅጥሮቿንም በማደስ፥ መሠረትዋንም በመጠገን ላይ ናቸው።
ዕዝራ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም ሽማግሌዎቹን፦ ‘ይህን ቤት እንድትሠሩ፥ ይህንንም ቅጥር እንድታድሱ ማን አዘዛችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛም መሪዎቹን፣ “ይህን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራትና ይህንም ውቅር ለመጠገን የፈቀደላችሁ ማን ነው?” ብለን ጠየቅናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛም የሕዝቡን መሪዎች ‘ይህን ቤተ መቅደስ እንደገና መልሳችሁ ለመሥራትና ቅጽሮቹንም ለማደስ ማን ፈቀደላችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያንም ሽማግሌዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘዛችሁ? የምትሠሩበትንስ ሥልጣን ማን ሰጣችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያንም ሽማግሌዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ፥ ይህንስ ቅጥር ታድሱ ዘንድ ያዘዛችሁ ማን ነው?’ ብለን ጠየቅናቸው። |
ከአንተ ዘንድ የመጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጡ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ዓመፀኛይቱንና ክፉይቱን ከተማ በመስራት፥ ቅጥሮቿንም በማደስ፥ መሠረትዋንም በመጠገን ላይ ናቸው።
ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁ አምላክ ቤትም እንደ ሄድን በንጉሡ ዘንድ ይታወቅ፥ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በጥንቃቄ ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል።