ዕዝራ 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፦ “ይህንስ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ስም ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም፣ “ይህን ሕንጻ የሚገነቡት ሰዎች ስም ማን ይባላል?” በማለት ጠየቋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የተባበሩአቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ለማወቅም ጠየቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም፥ “ይህችን ከተማስ የሚሠሩ ሰዎች ስም ማን ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፦ “ይህንስ ሥራ የሚሠሩት ሰዎች ስም ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው። |
ባስልኤል፥ ኤልያብና ጥበበኞች ሁሉ፥ የመቅደሱን አገልግሎት ሥራ ሁሉ እንዲያደርጉና እንዲያውቁ ጌታ ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው ጌታ ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ።