ሕዝቅኤል 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ ግንቡን ቦርቡረው አለኝ፥ ግንቡንም በቦረቦርሁት ጊዜ እነሆ አንድ መግቢያ አገኘሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ግንቡን ንደለው” አለኝ፤ እኔም ግንቡን ነደልሁት፤ አንድ በርም አገኘሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰው ልጅ ሆይ! በዚህ በኩል ግንቡን ሸንቊረው” አለኝ፤ በሸነቈርኩትም ጊዜ አንድ በር አገኘሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ግንቡን ንደለው” አለኝ፤ ግንቡንም በነደልሁት ጊዜ ደጃፍ አገኘሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ግንቡን ንደለው አለኝ፥ ግንቡንም በነደልሁት ጊዜ መዝጊያ አገኘሁ። |