በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ። ቀደም ሲል እግዚአብሔር በተናገረውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረው።
ሕዝቅኤል 7:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባዕድም እጅ ለዝርፊያ፥ በምድር ላሉ ክፉዎች እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እነርሱም ያረክሱአታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለባዕዳን ዝርፊያ፣ ለምድር ክፉዎችም ብዝበዛ አድርጌ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ያረክሱታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጌጦቻችሁን ለባዕዳን በምርኮ፥ ለምድር ኃጢአተኞችም በብዝበዛ መልክ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነርሱም ያረክሱታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባዕድም እጅ ለንጥቂያ፥ በምድር ኀጢአተኞችም እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ያረክሱአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባዕድም እጅ ለንጥቂያ፥ በምድር ኃጢአተኞችም እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣታለሁ፥ እነርሱም ያረክሱአታል። |
በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ። ቀደም ሲል እግዚአብሔር በተናገረውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረው።
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፥ እነዚያ በሰገነቶቻቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፥ እንደ ቶፌት ስፍራ የረከሱ ይሆናሉ።’ ”
ባዕዳን፥ የሕዝቦች ጨካኞች የሆኑ፥ ቆርጠው ጣሉት፤ በተራሮች እና በሸለቆዎች ሁሉ ውስጥ ቅርጫፎቹ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ፥ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ወጥተው ትተውት ሄዱ።