ሕዝቅኤል 47:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዙ በሚገባበት ስፍራ ያለ ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ ይህ ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ የባሕሩ ውኃ ይፈወሳል፥ ወንዙ በሚገባበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንዙ በሚፈስስበት ስፍራ ሁሉ ብዙ ሕያዋን ፍጥረታት ይኖራሉ። ይህ ውሃ በዚያ ስለሚፈስስና ጨውማ የሆነውን ውሃ ንጹሕ ስለሚያደርገው፣ ዓሣ በብዛት ይኖራል፤ ስለዚህ ወንዙ በሚፈስስበት ስፍራ ሁሉ ማንኛውም ነገር በሕይወት ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃው በሚፈስበት ስፍራ ሁሉ ልዩ ልዩ ዐይነት እንስሶችና ዓሣም በብዛት ይገኛል፤ የወንዙ ፈሳሽ በሙት ባሕር የሚገኘውን በማደስ ያጠራዋል፤ በሚፈስበትም ቦታ ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በሚገባበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፤ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፥ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፥ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፥ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል። |
እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።
ጌታም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።
እነርሱም በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ አሉትም “ወንድም ሆይ! በአይሁድ መካከል አምነው የነበሩት ስንት አእላፋት እንደ ሆኑ ታያለህ፤ ሁላቸውም ለሕግ የሚቀኑ ናቸው።
የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።