ሕዝቅኤል 47:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ አሁን ግን ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ ምክንያቱም ውሃው ስለ ሞላና ጥልቅ ስለ ነበረ፣ በዋና ካልሆነ በቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም አልፎ አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ ውሃው ጥልቅ ስለ ነበረ ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ እርሱም ሊራመዱበት የማይቻል ለዋና ግን በቂ ጥልቀት ነበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፤ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፥ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፥ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ። |
እንደገና አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ጉልበት ድረስ ነበር። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ድረስ ነበር።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”
ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም ማንም ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሰዎች ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤