La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 44:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለዓመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ርኩሰታችሁ ከእንግዲህ ሁሉ ያብቃ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለዐመፀኛው የእስራኤል ቤት እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አስጸያፊ ሥራችሁ ከእንግዲህ ያብቃ!

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ ለዐመፀኞቹ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ክፉ አድራጎታችሁን ሁሉ አስወግዱ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለዐ​መ​ፀ​ኛው ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ርኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ይብ​ቃ​ችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለዓመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 44:6
5 Referencias Cruzadas  

ግምባርህን ከባልጩት እንደሚጠነክር አልማዝ አድርጌዋለሁ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና አትፍራቸው፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል መሪዎች ሆይ፥ ይብቃችሁ፤ ግፍንና ጭቆናን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አንሱ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


አሕዛብ እንደሚያደርጉት በመዳራት፥ በሥጋዊ ምኞት፥ በስካር፥ በመሶልሶል፥ ያለ ልክ በመጠጣት፥ በአስነዋሪ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።