ሕዝቅኤል 43:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንጻቱንም ከፈጸምህ በኋላ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈንና ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ታቀርባለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንጻቱን ከፈጸምህ በኋላ፣ ከመንጋው እንከን የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንን ሁሉ ከፈጸምክ በኋላ ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ ከመንጋው ወስደህ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንጻቱንም ከፈጸምህ በኋላ ነውር የሌለበትን ወይፈን፥ ከበጎችም ነውር የሌለበትን ጠቦት በግ ታቀርባለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንጻቱንም ከፈጸምህ በኋላ ነውር የሌለበትን ወይፈን ከመንጋውም የወጣውን ነውር የሌለበትን አውራ በግ ታቀርባለህ። |
ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ለካህናት፥ ከሳዶቅ ዘር ለሆኑ ለሌዋውያን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።