ጌታም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጌታ ቤት ሥርዓት ሁሉ እና ሕጉን ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፤ የቤቱን መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።
ሕዝቅኤል 42:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነዚህም ክፍሎች በታች በስተ ምሥራቅ በኩል፥ ሰው ከውጭው አደባባይ የሚገባባት መግቢያ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከውጩ አደባባይ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ በስተምሥራቅ የታችኞቹ ክፍሎች መግቢያ ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታችኛዎቹ ክፍሎች በምሥራቅ በኩል ከወደ ውጪው አደባባይ መግቢያ ነበራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነዚህም ዕቃ ቤቶች በታች በስተምሥራቅ በኩል፥ ሰው ከውጭው አደባባይ የሚገባበት መግቢያ ነበረ፤ ይህም በቅጥሩ ራስ አጠገብ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነዚህም ዕቃ ቤቶች በታች በስተ ምሥራቅ በኩል፥ ሰው ከውጭው አደባባይ የሚገባባት መግቢያ ነበረ። ይህም በቅጥሩ ራስ አጠገብ ነበረ። |
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጌታ ቤት ሥርዓት ሁሉ እና ሕጉን ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ፤ የቤቱን መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።
በበሩ አጠገብ ባለው መግቢያ ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ለካህናት ወደሚሆን ወደተቀደሰው ክፍል አገባኝ፤ እነሆ በዚያ በምዕራብ በኩል በስተ ኋላ አንድ ስፍራ ነበረ።