ሕዝቅኤል 42:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ክፍሎች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ሲሆን በመቅደሱ ፊት ለፊት የነበሩት ክፍሎች ግን ርዝመታቸው መቶ ክንድ ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ከውጩ አደባባይ ቀጥሎ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ዐምሳ ክንድ ሲሆን፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በውጪው አደባባይ በኩል ያሉት ክፍሎች ኀምሳ ክንድ ርዝመት ሲኖራቸው ከቤተ መቅደሱ ትይዩ ያሉት ክፍሎች ግን መቶ ክንድ ርዝመት ነበራቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በመቅደሱ ፊት የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው መቶ ክንድ ሲሆን፥ በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ነበረና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በመቅደሱ ፊት የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው መቶ ክንድ ሲሆን በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ነበረና። Ver Capítulo |