ሕዝቅኤል 40:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበሮቹ አጠገብ የነበረው ወለል ርዝመት እንደ በሮቹ መጠን ነበረ፤ ይህም ታችኛው ወለል ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታችኛው ንጣፍ ወለል ከመግቢያው በር ጋራ ተያይዞ የተሠራ ሲሆን፣ ስፋቱ እንደ በሮቹ ርዝመት መጠን ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የድንጋዩም ንጣፍ እስከ አደባባዩ ዙሪያ ይዘልቃል፤ የውጪውም አደባባይ ከውስጠኛው አደባባይ ዝቅ ያለ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወለሉም በበሮች አጠገብ ነበረ፤ ይህም ታችኛው ወለል እንደ በሮቹ ርዝመት መጠን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወለሉም በበሮች አጠገብ ነበረ ይህም ታችኛው ወለል እንደ በሮቹ ርዝመት መጠን ነበረ። |