ሕዝቅኤል 40:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጓዳዎቹም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ ጓዳውም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእያንዳንዱ ዘብ ቤት ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ የግንብ ዐጥር አለ፤ የዘብ ቤቶቹም ስፋት እኩል በኩል ስድስት ክንድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእያንዳንዱ ማረፊያ ክፍል ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ ውፍረቱም አንድ ክንድ የሆነ ዝቅተኛ ግንብ ነበር፤ ክፍሎቹም የአራት ማእዘን ቅርጽ ያላቸው ሆነው እያንዳንዱ ማእዘን ስድስት ክንድ ርዝመት ነበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዕቃ ቤቱም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ፥ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ የዕቃ ቤቱም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዘበኛ ጓዳዎችም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፥ የዘበኛ ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበሩ። |
ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ ትናንሽ መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ደግሞም በመተላለፊያው ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
ጓዳዎቹ፥ የግንቡ አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከሌሎቹ ጋር እኩል መጠን ነበራቸው፤ በእርሱና በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱ ደግሞ ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።
ክፍሉም ርዝመቱ አንድ ዘንግ፥ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በክፍሎቹ መካከል ያለው ርቀት አምስት ክንድ ነበረ፤ ከበራፉም በውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ መተላለፊያ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።