Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 40:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዕቃ ቤቱም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ፥ በዚ​ያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ የዕቃ ቤቱም በዚህ በኩል ስድ​ስት ክንድ በዚ​ያም በኩል ስድ​ስት ክንድ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በእያንዳንዱ ዘብ ቤት ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ የግንብ ዐጥር አለ፤ የዘብ ቤቶቹም ስፋት እኩል በኩል ስድስት ክንድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በጓዳዎቹም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ ጓዳውም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በእያንዳንዱ ማረፊያ ክፍል ፊት ለፊት ከፍታው አንድ ክንድ ውፍረቱም አንድ ክንድ የሆነ ዝቅተኛ ግንብ ነበር፤ ክፍሎቹም የአራት ማእዘን ቅርጽ ያላቸው ሆነው እያንዳንዱ ማእዘን ስድስት ክንድ ርዝመት ነበረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በዘበኛ ጓዳዎችም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ በዚያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፥ የዘበኛ ጓዳዎቹም በዚህ በኩል ስድስት ክንድ በዚያም በኩል ስድስት ክንድ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 40:12
6 Referencias Cruzadas  

የበ​ሩ​ንም መግ​ቢያ ወርድ ዐሥር ክንድ፥ የበ​ሩ​ንም ርዝ​መት ዐሥራ ሦስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


ከአ​ን​ዱም የዕቃ ቤት ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበ​ሩን ወርድ ሃያ አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ በሩና በሩም ትይዩ ነበረ።


በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።


እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


በበ​ሮ​ቹም በግ​ንቡ አዕ​ማድ አጠ​ገብ ዕቃ ቤቱና መዝ​ጊ​ያው ነበሩ፤ በዚ​ያም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያጥቡ ነበር።


የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝ​መት አንድ ዘንግ፤ ወር​ዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም፤ በስ​ተ​ው​ስጥ በኩል የሚ​ገኝ የበሩ የመ​ድ​ረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos