ሕዝቅኤል 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም የኃጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀኖች ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፥ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ኀጢአት ባደረጉባቸው ዓመታት መጠን የቀን ቍጥር መድቤብሃለሁ። ስለዚህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን የእስራኤልን ቤት ኀጢአት ትሸከማለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ኃጢአት በሠሩባቸው ዓመቶች ብዛት ቀኖችን መድቤልሃለሁ፤ ይህም አንድ ቀን ለአንድ ዓመት ማለት ነው፤ ስለዚህ ለሦስት መቶ ዘጠና ቀኖች የእስራኤላውያንን ኃጢአት ትሸከማለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም የኀጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀን ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፤ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም የኃጢአታቸውን ዓመታት ለአንተ የቀን ቍጥር እንዲሆንልህ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ሰጥቼሃለሁ፥ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት ትሸከማለህ። |
ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ እያንዳንዱም ቀን እንደ አንድ ዓመት ሆኖ፥ በደላችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ መከፋቴንም ታውቃላችሁ።’