በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
ሕዝቅኤል 36:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአላፊ አግዳሚው ሁሉ ዐይን ባድማ የነበረች፥ ባድማዋ ምድር ትታረሳለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐላፊ አግዳሚው ዐይን ጠፍ ሆኖ ይታይ የነበረው ባድማ መሬት ይታረሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሻዎቻችሁ በኩል በሚያልፉ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ባድማ ሆና ትቈጠር የነበረችው ምድር ትታረሳለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባድማ የነበረች፥ በመንገደኛም ሁሉ ዐይን ዘንድ ባድማ የነበረች ምድር ትታረሳለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባድማ የነበረች በመንገደኛም ሁሉ ዓይን ዘንድ ባድማ የነበረች ምድር ትታረሳለች። |
በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
“ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆነች፤ የወደሙት፥ ባድማ የሆኑት፥ የፈረሱት ከተሞች አጥር ተሰርቶላቸዋል፥ መኖሪያም ሆነዋል” ይላሉ።
እጄንም በእነሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዲብላ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።