ሕዝቅኤል 33:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአትን ቢሠራ በእነርሱ ይሞታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ክፉ ቢሠራ፣ ይሞትበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጻድቅ ሰው የጽድቅ ሥራውን ትቶ ክፉ መሥራትን ቢጀምር፥ ስለ ክፉ ሥራው ይሞታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ኀጢአትን ቢሠራ ይሞትበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአትን ቢሠራ ይሞትባታል። |
ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።
ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።