ሕዝቅኤል 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ ገመድ ያደርጉብሃል፥ ከእነሱም ጋር ያስሩሃል፥ ከመካከላቸውም አትወጣም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ፣ የሰው ልጅ ሆይ፤ በገመድ ይጠፍሩሃል፤ ወጥተህም በሕዝብ መካከል እንዳትመላለስ ያስሩሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ልጅ ሆይ! በገመድ ስለምትታሰር ወደ አደባባይ መውጣት አትችልም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ! እነሆ ገመድ ያደርጉብሃል፤ ያስሩህማል፤ አንተም ከመካከላቸው አትወጣም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ ገመድ ያደርጉብሃል ያስሩህማል፥ አንተም በመካከላቸው አትወጣም፥ |
እውነት እውነት እልሃለሁ፤ አንተ ጎልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ቦታ ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፤ ሌላ ሰውም ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል” አለው።