La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 29:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእጅህ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህ ትከሻቸውን ሁሉ ቆረጥህ፤ በአንተ ላይ ሲደገፉ ተሰበርህ ወገባቸውንም ሁሉ አንቀጠቀጥህ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእጃቸው ሲይዙህ ተሰንጥረህ ትከሻቸውን ወጋህ፤ ሲደገፉህም ተሰብረህ ጀርባቸውን አጐበጥህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእጆቻችሁ በያዙአችሁ ጊዜ ተሰነጣጥቃችሁ ትከሻቸውን ወጋችሁ፤ በእናንተ ላይ በተደገፉ ጊዜ እናንተ ተሰብራችሁ ወገባቸው ተብረከረከ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእጅ በያ​ዙህ ጊዜ ተሰ​በ​ርህ፤ ጫን​ቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አቈ​ሰ​ልህ፤ በተ​ደ​ገ​ፉ​ብ​ህም ጊዜ ተሰ​በ​ርህ፤ ወገ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አን​ቀ​ጠ​ቀ​ጥህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእጅ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህ ጫንቃቸውንም ሁሉ አቈሰልህ፥ በተደገፉብህም ጊዜ ተሰበርህ ወገባቸውንም ሁሉ አንቀጠቀጥህ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 29:7
14 Referencias Cruzadas  

የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ፥ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኰዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቆስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው’ ሲል የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይጠይቅሃል።”


ከሃዲን ሰው በመከራ ጊዜ መተማመን እንደ ተሰበረ ጥርስና እንደ ሰለለ እግር ነው።


እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ፤ ያፍራሉም።


ስለዚህ የፈርዖን ኃይል እፍረት፥ በግብጽም ጥላ መታመን ስድብ ይሆንባቸዋል።


እነሆ፥ በዚህ በተቀጠቀጠ የሸንበቆ በትር በግብጽ ተማምነሀል፤ ሰው ተማምኖ ቢመረኰዘው እጁን ወግቶ ያቈስለዋል፤ የግብጽ ንጉሥ ፈርኦን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።


ፌ። ዓይናችን ወደ ከንቱ ረዳታችን ገና ሲመለከት ጠፍቶአል፥ በመቆየታችን ማዳን የማይቻለውን ሕዝብ ጠብቀናል።


ከእንግዲህ ወዲያ ለእስራኤል ቤት መታመኛ አይሆንም፥ እነርሱን በተከተሉ ጊዜ በደልን ያሳስባል፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ሆኖም ግን ተማርካ ተወሰደች፤ ሕፃናቶችዋ በመንገዶች ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፤ በከበርቴዎችዋ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።


ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኃይልዋ ነበሩ፤ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ።