La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 28:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በገዳይህ ፊትም፦ “እኔ አምላክ ነኝ” ትላለህን? ቢሆንም አንተ በገዳይህ እጅ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታዲያ በገዳዮችህ ፊት፣ “አምላክ ነኝ” ትላለህን? በገዳዮችህ እጅ ስትገባ፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታዲያ ሊገድሉህ በሚመጡበት ጊዜ አሁንም ራስህን እንደ አምላክ ትቈጥር ይሆን? በገዳዮችህ እጅ ወድቀህ ስትገኝ ሰው እንጂ አምላክ ያለመሆንህ ይታወቃል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንተ ሰው ስት​ሆን ለሚ​ገ​ድ​ሉህ ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለ​ህን? ሰው ነህ እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በውኑ በገዳይህ ፊት፦ እኔ አምላክ ነኝ ትላለህን? ነገር ግን በገዳይህ እጅ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 28:9
10 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።


ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ ጌታ እጁን በሚዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።


እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፤ በእርሷና በሴቶች ልጆቿ ትዕቢት፥ የምግብ ጥጋብ፥ የበለጸገ ምቾት ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።


በባዕዳን እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል አንተም እንዲህ ብለሃል፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ በእግዚአብሔር ወንበር በባሕር ልብ ተቀምጫለሁ፤ ነገር ግን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


ወደ ጉድጓድ ያወርዱሃል፤ በባሕር ልብ ተገድለው በሞቱበት ሞት ትሞታለህ።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።