Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 28:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ወደ ጉድጓድ ያወርዱሃል፤ በባሕር ልብ ተገድለው በሞቱበት ሞት ትሞታለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ወደ ጕድጓድ ያወርዱሃል፤ በጥልቁም ባሕር ውስጥ፣ በባሕሮችም ልብ ውስጥ አስከፊ ሞት ትሞታለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንተን ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ይጥሉሃል፤ በባሕሩም መካከል አሠቃቂ የሆነ ሞት ትሞታለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ወደ ጕድ​ጓድ ያወ​ር​ዱ​ሃል፤ በሰ​ይ​ፍም ትሞ​ታ​ለህ፤ ሬሳ​ህ​ንም ወደ ባሕር ይጥ​ሉ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ወደ ጕድጓድ ያወርዱሃል፥ ተገድለው እንደ ሞቱ በባሕር ውስጥ ትሞታለህ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 28:8
17 Referencias Cruzadas  

በጥልቅ ውኆች ውስጥ፥ በባሕር በተሰበርሽ ጊዜ ግን ሸቀጣ ሸቀጥሽና በመካከልሽ ያሉ ጉባኤሽ ሁሉ ወድቀዋል።


እነሆ፥ ታላቅ ምሬት ለደኅንነቴ ምክንያት ሆነ፤ አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጉድጓድ አዳንካት፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልህ።


የሰው ደም ያለበት ሰው እስከጉድጓድ ይሸሻል፥ ማንም አያስጠጋውም።


“በሙሉ ሕይወት እያሉ፥ ከነነፍሳቸው፥ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፥ ወደ ጉድጓድ እንደሚወድቁም ይሁኑ፥


መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ፥ በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን።


አቤቱ፥ ወደ አንተ ጠራሁ፥ ወደ አምላኬም ለመንሁ።


የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ እጠራለሁ፥ ዝም ብትለኝ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልመስል፥ አንተ ዓለቴ ሆይ፥ ዝም አትበለኝ።


ነፍሴ ወደ መቃብር እንዳትወርድ አድኖአታል፥ ሕይወቴም ብርሃንን ታያለች ይላል።”


ነፍሱን ከጉድጓድ፥ በሰይፍም እንዳይጠፋ ሕይወቱን ይጠብቃል።”


ወደ ሲኦል ይወርዳልን? አብረን ወደ አፍር ውስጥ እንገባ የለምን?”


ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።


ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።


ሀብትሽን ይዘርፋሉ፥ ሸቀጣ ሸቀጥሽንም ይበዘብዛሉ፤ ቅጥርሽን ያፈርሳሉ፥ የተዋቡ ቤቶችሽን ያጠፋሉ፤ ድንጋይሽን፥ እንጨትሽንና አፈርሽን በውኆች መካከል ያስቀምጣሉ።


በገዳይህ ፊትም፦ “እኔ አምላክ ነኝ” ትላለህን? ቢሆንም አንተ በገዳይህ እጅ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios