ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ።
ሕዝቅኤል 23:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየቻቸው ወዳጆችሽን አስነሣብሻለሁ፥ እነርሱንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ፣ ኦሖሊባ ሆይ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጠልተሻቸው ከእነርሱ ዘወር ያልሽውን ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁንም ኦሆሊባ ሆይ! እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምልሽ ይህ ነው፤ እነዚያን ወዳጆችሽን ተጸይፈሻቸዋል፤ ነገር ግን እነርሱ በአንቺ እንዲነሡ አደርጋለሁ፤ እንዲከቡሽም ወደዚህ አመጣቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ሐሊባ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ወዳጆችሽን አስነሣብሻለሁ፤ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ፥ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ። |
ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ።
እነርሱም የባቢሎን ልጆች፥ ከለዳውያን ሁሉ ፋቁድ፥ ሾዓ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር የአሦር ልጆች ሁሉ፥ ሁሉም መልከ መልካም ወጣቶች፥ ገዢዎች፥ ባለ ሥልጣናት፥ መኰንኖችና የተጠሩ፥ ሁሉም ፈረስ የሚጋልቡ ናቸው።
ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ይበዘብዟታል፥ ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል።