ሕዝቅኤል 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ጌታ ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ደግሞ ወደ ሰገባው አይመለስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝሁት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ሕዝቡ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ወደ ሰገባው አይመለስም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን እንደ መዘዝኩና መልሼም ወደ አፎቱ እንደማልከተው ሰው ሁሉ ያውቃል።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ያውቃል፤ እርሱም ደግሞ አይመለስም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ያውቃል፥ እርሱም ደግሞ አይመለስም። |
አንተም፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምልከው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፥ ስከሩም፥ አስታውኩም፥ ውደቁም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው።