ትልልቅ ክንፎችና ብዙ ላባ ያለው ሌላ አንድ ትልቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም ይህ ወይን እንዲያጠጣው ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ፥ ቅርንጫፉንም ከተተከለበት ከመደብ ወደ እርሱ ሰደደ።
ሕዝቅኤል 17:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅርንጫፍ እንዲያወጣ፥ ፍሬ እንዲያፈራ፥ የተዋበ ወይን እንዲሆን ብዙም ውኃ ባለበት በመልካም መሬት ውስጥ ተተክሎ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅርንጫፍ እንዲያወጣ፣ ፍሬ እንዲያፈራና ያማረ የወይን ተክል እንዲሆን በአጠገቡ ብዙ ውሃ ባለበት በመልካም መሬት ተተክሎ ነበር።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የወይኑ ተክል እንደገና የተተከለው ቅጠሉ በሚገባ ለምልሞ ፍሬ በማፍራት የተዋበ ተክል መሆን በሚችልበት በቂ ውሃ ባለበት ስፍራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐረግም ያወጣ፥ ፍሬም ያፈራ፥ የከበረ ወይንም ይሆን ዘንድ በመልካም መሬት ውስጥ፥ በብዙም ውኃ አጠገብ ተተክሎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አረግም ያወጣ ፍሬም ያፈራ የከበረም ወይን ይሆን ዘንድ በመልካም መሬት ውስጥ በብዙም ውኃ አጠገብ ተተክሎ ነበር። |
ትልልቅ ክንፎችና ብዙ ላባ ያለው ሌላ አንድ ትልቅ ንስር ነበረ፥ እነሆም ይህ ወይን እንዲያጠጣው ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ፥ ቅርንጫፉንም ከተተከለበት ከመደብ ወደ እርሱ ሰደደ።
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያድግ ይሆንን? እንዲደርቅ፥ አዲስ የበቀለው ቅጠሉም እንዲጠወልግ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አያረግፈውምን? ከሥሩም ለመንቀል ብርቱ ክንድ ወይም ብዙ ሕዝብ አያስፈልገውም።