ሕዝቅኤል 17:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያድግ ይሆንን? እንዲደርቅ፥ አዲስ የበቀለው ቅጠሉም እንዲጠወልግ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አያረግፈውምን? ከሥሩም ለመንቀል ብርቱ ክንድ ወይም ብዙ ሕዝብ አያስፈልገውም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 “እንዲህም በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ያድግ ይሆን? ይጠወልግ ዘንድ ሥሩ ተነቅሎ ፍሬው አይረግፍምን? ቀንበጡም ሁሉ ይደርቃል። ከሥሩ ለመንቀል ብርቱ ክንድና የብዙ ሰው ጕልበት አያስፈልገውም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር፦ ይህ የተተከለው የወይን ተክል ይጸድቃልን? የመጀመሪያው ንስር ሥሩን ነቅሎ ፍሬው እንዲበሰብስና እንዲደርቅ እንዲሁም ለምለም ቅጠሉ እንዲጠወልግ አያደርገውምን? ሥሩን ለመንቀል ጠንካራ የጦር መሣሪያ ወይም ኀይለኛ ሠራዊት አያስፈልገውም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ ይከናወንለት ይሆን? ይደርቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበቀለውስ ቅጠሉ ይጠወልግ ዘንድ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አይለቅመውምን? ሥሩም የተነቀለው በብርቱ ክንድና በብዙ ሕዝብ አይደለም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይደርቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበቀለውስ ቅጠሉ ይጠወልግ ዘንድ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አይለቅመውምን? ሥሩም የተነቀለው በብርቱ ክንድና በብዙ ሕዝብ አይደለም። Ver Capítulo |