ሕዝቅኤል 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንኰራኵሮችም እኔ እየሰማሁ “የሚሽከረከሩ መንኰራኵሮች” ተብለው ተጠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንኰራኵሮቹም፣ “ተሽከርካሪ መንኰራኵሮች” ተብለው ሲጠሩ ሰማሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንኰራኵሮቹም እኔ እየሰማሁ የሚሽከረከሩ መንኰራኩሮች ተብለው ተጠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራቱም መንኰራኵሮች እኔ እየሰማሁ ጌልጌል ተብለው ተጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንኰራኵሮችም እኔ እየሰማሁ ጌልጌል ተብለው ተጠሩ። |
እያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፥ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፥ ሦስተኛው ፊት የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም ፊት የንስር ፊት ነበረ።
በፍታም የለበሰውን ሰው እንዲህ አለው፦ በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትናት ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ።