ሕዝቅኤል 1:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማዩም በታች ክንፎቻቸው የአንዱ ወደ ሌላው ተዘርግተው ነበር፥ እያንዳንዱም ገላውን የሚሸፍንበት ሁለት ክንፎች ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጠፈሩም በታች የአንዱ ክንፍ ወደ ሌላው ተዘርግቶ ነበር፤ እያንዳንዱም ሰውነቱን የሚሸፍንበት ሁለት ክንፍ ነበረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወለሉም ሥር እያንዳንዱ እንስሳ ከጐኑ ባለው ፍጥረት አንጻር ሁለት ክንፎቹን ዘርግቶ፥ በቀሩትም ሁለት ክንፎቹ ሰውነቱን ሸፍኖ ቆሞ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጠፈሩም በታች ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተቃንተው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ገላውን የሚከድኑ ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጠፈሩም በታች ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተቃንተው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ገላውን የሚከድኑ ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሩት። |
ሲሄዱም የክንፎቻቸውን ድምፅ እንደ ብዙ ውኆች ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል አምላክ ድምፅ፥ እንደ ማዕበል ድምፅ፥ እንደ የታላቅ ሠራዊት ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።