ሕዝቅኤል 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጀርባቸውም ረዥምና የሚያስፈራ ነበር፥ የአራቱም ጀርባቸው ዙሪያው በዐይኖች ተሞልቶ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመንኰራኵሮቹ ክብ ጠርዝ ረዥምና አስፈሪ ነበር፤ የአራቱም መንኰራኵሮች ክብ ጠርዝ ዙሪያውን በዐይኖች የተሞላ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመንኰራኲሮቹም ጠርዝ ግዙፍና የሚያስፈራ ነበር፤ አራቱም የመንኰራኲር ጠርዝ ዙሪያቸውን በዐይን የተሞሉ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራቱ ዙሪያ ሁሉ ዐይኖችን የተመላ ጀርባቸውን አየሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቁመታቸውም የረዘመና የሚያስፈራ ነበረ፥ የአራቱም ክበብ ዙሪያው በዓይን ተሞልቶ ነበር። |
የዚህን የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን አይተው ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የጌታ ዐይኖች ናቸው።”
በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።
አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር።