ዘፀአት 8:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም፦ “እነሆ እኔ ከአንተ ዘንድ እወጣለሁ፥ የዝንቡም መንጋ ከፈርዖን፥ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ነገ እንዲሄዱ ወደ ጌታ እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ለጌታ ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እንዳይለቅቅ ፈርዖን እንደገና አያታልለን” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ “ሂዱና በዚሁ ምድር ለአምላካችሁ ሠዉ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጉሡ ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ሄዳችሁ በዚህች አገር ውስጥ ለአምላካችሁ መሥዋዕት አቅርቡ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ በዚያች ምድር ለአምላካችሁ ሠዉ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ በአገሩ ውስጥ ለአምላካችሁ ሠዉ፤” አላቸው። |
ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፥ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁትም ጌታን አገልግሉ፤
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።