ዘፀአት 8:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤን ባትለቅቅ፥ እነሆ በአንተ ላይ፥ በአገልጋዮችህ ላይ፤ በሕዝብህ ላይ፥ በቤቶችህም ላይ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብፃውያንም ቤቶች፥ የቆሙባትም ምድር ሁሉ በዝንብ መንጋ ይሞላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፣ አሮን በትሩን እንደ ያዘ እጁን ሲዘረጋና የምድሩን ትቢያ ሲመታ፣ በግብጽ ምድር ያለው ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ። ሰውንም ሆነ እንስሳውን ተናካሽ ትንኝ ወረረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደተባሉትም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታ፤ በግብጽ አገር ያለውም ትቢያ ሁሉ ወደ ተናካሽ ትንኝነት ተለወጠ፤ ሰዎችንና እንስሶችንም ሁሉ ሸፈነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም እጁን ዘረጋ፤ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ የምድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፤ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታው፤ በሰውና በእንስሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግብፅ አገር ሁሉ የምድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ። |
ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’”
ጌታም ሙሴን አለው፦ “ማልደህ ተነሣ፥ በፈርዖንም ፊት ቅረብ፤ እነሆ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ።