ዘፀአት 6:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በጌታ ፊት፦ “እነሆ እኔ ከንፈሬ ያልተገረዘ ነኝ፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ግን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ፈርዖን ምን ብሎ ይሰማኛል? አንደበቴ ኰልታፋ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ግን “እኔ ኰልታፋ ነኝ፤ ታዲያ፥ ንጉሡ እንዴት ሊሰማኝ ይችላል?” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት፥ “እነሆ፥ እኔ አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት፦ “እነሆ እኔ ከንፈረ ቈላፍ ነኝ፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል?” አለ። |
ሙሴም ጌታን፦ “ጌታ ሆይ፥ እኔ አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባርያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፌንና ምላሴን ይይዘኛል።”
ሙሴም በጌታ ፊት፦ “እነሆ የእስራኤል ልጆች አልሰሙኝም፤ ታድያ እንዴት ፈርዖን ይሰማኛል? እኔ ደግሞ ከንፈሬ ያልተገረዘ ሰው ነኝ” ብሎ ተናገረ።
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።